የኔዋ cover art

የኔዋ

by Anu

AI-generated Folk song · 3:23 · 3 plays

Lyrics

የልቤን ብነግርሽ በግልፅ አውጥቼ
ደጅሽን ጠናሁት ክብሬን አሳልፌ
ላንቺ የነበረኝ ያ ፍቅሬ ጥልቀቱ
ዛሬ ግን ሆነብኝ የዝምታ እራቱ።
ሰው ምን ያውቅልኛል ውስጤን ካላየው
ያንን ሁሉ ሰቆቃ እንዴት ልቻለው?
ባጃጅ ላይ ስባዝን ውሎና አዳሬ
ላንቺ ነው ነበረ የሁሉ ግብሬ
እቤትም አውርቼ ሽማግሌ ልልክ
ቀጠሮ ይዤ ነበር ወደ አንቺ ልመጣ ልዘልቅ።
አንቺ ግን ሸሸሽኝ በሰው ምክር ሆነሽ
የገነባሁትን ፍቅር በዝምታ አፈረስሽ።
ፍቅር ማለት እንዲህ መሸሽ ነበረ ወይ?
የልብን ደብቆ በሰው ማየት ወይ?
ወፈር ባለው ድምፄ ስምሽን ስጠራው
ላንቺ ያለኝ ቦታ ከምንም በላይ ነው።
ግን ዝምታሽ ነሲ እኔን ያደማኛል
ከፍቅር ይልቅ መለያየት ይቀድማል።
የሰማሁት ሁሉ ጆሮዬን ቢያመውም
አሁንም ዝምታሽ መልስ አልሆነኝም
"ምን እለዋለሁ?" ብለሽ ብትጨነቂም
እኔን ግን መራቁን መንገድ አረግሺው።
እውነቱ ሲወጣ ጥፋቱ ሲገለጥ
የኔ ፍቅር ነበር ላንቺ የሚከብድሽ የሚበልጥ።

**[Outro]**
ተለያየን ካልሽኝ ውሳኔሽ ከሆነ
ያንቺ መጥፋት እኔን ክፉኛ አዘለለ
ክብሬን ጠብቄ መንገዴን እሄዳለሁ
በዝምታሽ ፈንታ ዝምታን እመርጣለሁ።

More by Anu

Make your own song with SoundLab AI · Turn your own lyrics into a song