
Yene Fkr
Lyrics
የኔ ፍቅር
የኔ ፍቅር
የኔ ፍቅር
ግልፅ ነው ይታያል ፣ ላፍታ ማይጋረድ
ምንም አይገድበው ፣ የኔ አንቺን መውደ፣
አንቺን አንቺን ይላል ፣ የልቤ መአዛ
ሰርፀሽ ሰፍረሽዋል ፣ መውደድሽ ሲበዛ።
ፍቅር መላመድ ነው
የሚባለው ፈሊጥ ፣ ውሸት ኖሯል ለካ
መዋሀድ ነው ፍቅር
አንዱን የሚሰማው ፣ አንዱ ከተነካ፣
ከመላመዱ'ማ
ሁለት መሆናቸው ፣ ያሳያል ከቃሉ
መወሀድ ነው እንጂ
በቃ አንድ መሆን ፣ ሁለት ናቸው ሲሉ።
እና የኔ ፍቅር
ተዋህደሻል ከኔ ፣ በፍቅር በመውደድ
ጨርቅን በሚያስጥለው ፣ በደስታ ለማበድ፣
ሁለመና ውቢት ፣ የግል የብቻዬ
ትናንት ዛሬም ነገም ፣ ትንፋሽ ተካፋዬ።