FattyD cover art

FattyD

by Fitsum Debebe

AI-generated Funk song · 3:48 · 3 plays

Lyrics

እኔም እሷ ትብስ ፣ አንቺም እሱ ይብስ
ስንባባል ከርመን ፣ ጥላቻን ስንጥስ፣
ልክ ያልነበረበት ፣ ከምንም የፀና
ተፋቅረን ነበረ ፣ የዛሬ አይሁንና።

ነበረ
ልቤ ያነገሰሸ ፣ ከፍ ባለ ዙፋን
ነበረ
ፍቅርሽ የሚያኖረን ፣ ሲቸግር ሲከፋን፣
ነበረ
ፉክክር የሌለው ፣ የግልሽ የብቻሽ
ነበረ
ልቤ ሌላ አላየም ፣ ነበር መጫወቻሽ።

ፍቅር ጠግበሽ ነው ወይ ፣ ከብዶሽ መሸከሙ
ከፍ ዝቅ ሚያረግሽ ፣ ያ ጣፋጭ ህመሙ?
በሕልም በሀሳብ ፣ በፍቅርሽ ታስሬ
ስናኝ በሰመመን ፣ አብቅቷል መኖሬ።

"ከሠጠሁት ፍቅር ፣ ካሳየሁት አሳር፣
ከቶ አይረሳኝም ፣ ካሳለፍነው አንፃር!
"ልርሳት" ቢልም እንኳን ፣ በሒደት ያረጃል
የመርሳት መንገዱ ፣ ዕድሜውን ይፈጃል!"

እያልሽ ታስቢያለሽ...
እያልሽ ታደቢያለሽ...

ከንቱ ነው ሐሳብሽ፣ከንቱ ነው ድካምሽ
እንደውም እንደውም ማን ነበረ ሥምሽ?

_______________________________

እኔም እሷ ትብስ ፣ አንቺም እሱ ይብስ
ስንባባል ከርመን ፣ ጥላቻን ስንጥስ፣
ልክ ያልነበረበት ፣ ከምንም የፀና
ተፋቅረን ነበረ ፣ የዛሬ አይሁንና።

ነበረ
ልቤ ያነገሰሸ ፣ ከፍ ባለ ዙፋን
ነበረ
ፍቅርሽ የሚያኖረን ፣ ሲቸግር ሲከፋን፣
ነበረ
ፉክክር የሌለው ፣ የግልሽ የብቻሽ
ነበረ
ልቤ ሌላ አላየም ፣ ነበር መጫወቻሽ።

ፍቅር ጠግበሽ ነው ወይ ፣ ከብዶሽ መሸከሙ
ከፍ ዝቅ ሚያረግሽ ፣ ያ ጣፋጭ ህመሙ?
በሕልም በሀሳብ ፣ በፍቅርሽ ታስሬ
ስናኝ በሰመመን ፣ አብቅቷል መኖሬ።

"ከሠጠሁት ፍቅር ፣ ካሳየሁት አሳር፣
ከቶ አይረሳኝም ፣ ካሳለፍነው አንፃር!
"ልርሳት" ቢልም እንኳን ፣ በሒደት ያረጃል
የመርሳት መንገዱ ፣ ዕድሜውን ይፈጃል!"

እያልሽ ታስቢያለሽ...
እያልሽ ታደቢያለሽ...

ከንቱ ነው ሐሳብሽ፣ከንቱ ነው ድካምሽ
እንደውም እንደውም ማን ነበረ ሥምሽ?

More by Fitsum Debebe

Make your own song with SoundLab AI